Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ ላገኙ ምሩቃን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግ ላገኙ ምሩቃን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ዛሬ የምክትል መቶ አለቃነት ማዕረግን ያገኛችሁ ምሩቃን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
በቀጣይ ጉዟችሁ፣ ከሀገር ፍቅር የመነጨ ዓላማ እና በየዕለቱ የሚዳብር የማይነጥፍ ዕውቀት እንድታዳብሩ አደራ እላለሁ ሲሉም አሳስበዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

ጀግንነት ከኢትዮጵያዊ ማንነት የተወረሰ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ÷ከእያንዳንዱ ተመራቂ መኮንንም ከኢትዮጵያዊ ማንነት የተቀዳ ጀግንነት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ69ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ወታደራዊ እጩ መኮንኖች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.