Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ባላይ መመዝበሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ ጥናት አመላከተ።
ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው በዚህ ጥናት ከ370 ቢሊየን ብር በላይ በባንኮች ላይ ማጭበርበር ተሞክሮ እንደነበር ተመላክቷል።
ጥናቱን ተከትሎ የፍትህ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የተለያዩ ባንኮች ፕሬዚዳንቶች፣ የኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
ጥናቱ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች መንስኤዎቻቸው እና የአፈጻጸም ዘዴያቸውን በመለየት የመፍትሔ ሃሳቦችን ለማቅረብ በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውይይቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮችን ባነጣጠረ የማጭበርበር ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን የተደረገው ጥናት አመላክቷል።
የባንክ ማጭበርበር ከተፈፀመባቸው 16 ባንኮች 50 በመቶው ወይም 961 ሚሊየን ብሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተፈፀመ መሆኑ በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም 17 በመቶው ወይም 329 ሚሊየን ብር የሚጠጋው በአቢሲኒያ ባንክ እንዲሁም 8 ነጥብ 5 በመቶ ወይም 162 ሚሊየን ብር የሚሆነው በኦሮሚያ ባንክ ላይ የተፈፀመ ነው ተብሏል።
በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር መንስኤዎች እና ወንጀሎች መንስኤያቸውን በመለየት የመፍትሄ ሀሳቦችን ለማቅረብ የተዘጋጀው ጥናት የሚፈፀሙት ወንጀሎች ለህዝብ ይፋ የሆኑ፣ በባንክ ብቻ የሚታወቀው እና የማይታወቁ የማጭበርበር ወንጀሎች መፈፀማቸውን አመላክቷል።
የማጭበርበር ወንጀሎቹ በባንኮች አስተዳደር አካላት የባንክ ሰራተኞች በሶስተኛ ወገን የሚፈፀሙ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ፡-

https://www.youtube.com/watch?v=ixBLrFWvo3o
በሚፈፀሙት ወንጀሎችም የኢትዮ-ቴሌኮም ሰራተኞች ጭሞር እንደሚሳተፉ የተደረገው ጥናት አመላክቷል፡፡
በጸጋዬ ወንደሰን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.