Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢ ኤስ ዲ፣ ውመን ኢምፓወርመንት አክሽን እና ህይወት ኢትዮጵያ የተባሉ በጎ አድራጊ ድርጅቶች በጋራ በመሆን ለተፈናቃይ ወገኖች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ የምግብ፣ የአልባሳትና በጦርነት ለተጎዱ ስድስት ትምህርት ቤቶች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ድርጅቶቹ ደብረብርሃን፣ ቀወት፣ ኤፍራታና ግድም፣ ደብረሲና፣ ሸዋሮቢትና አጣዬ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ነው ድጋፍ ያደረጉት።

የህይወት ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አለም ካሳ÷ በጦርነትና በግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ የግድ በመሆኑ የአደጋ ጊዜ ፕሮጀክት በመንደፍ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡

ከችግሩ ስፋት አንፃርም ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት ፡፡

ድጋፉን የተቀበሉት የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ ደረጀ ይንገሱ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ በዞኑ የተፈናቃዮች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ ሌሎች ድርጅቶችም በዚህ ተግባር እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘላለም ገበየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.