Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ መንግስት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል -ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡
የክልሉን የ2014/2015 ዓ.ም ምርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችና ቀጣይ ተግባራትን የተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ ላይ የተገኙት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉ መንግስት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ለቀጣይ የመኸር ወቅት የተሻለ ምርት ለማግኘት አመራሩ ለአርሶ አደሩ የተቀናጀ ድጋፍ እንዲያደርግ ማሳሰባቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው እንደገለጹት÷ በ2014/2015 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን 143 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.