Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱን አስታወቀ 

 

አዲስ አበባ፣ግንቦት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ወታደራዊ መንግስት በሀገሪቱ በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ተግባራዊ ሲደረግ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማንሳቱን አስታውቋል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት መሪ ጀኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን በሰጡት መግለጫ ባለፈው ዓመት ጥቅምት 25 በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ማዘዛቸውን ገልፀዋል፡፡

የሱዳን ሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት በበኩሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት የተወሰነው በሽግግሩ ወቅት በሀገሪቱ የተፈጠረው ውጥረት እንዲረግብ እና ውይይቶችን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር መሆኑን አመላክቷል፡፡

የሀገሪቱ የፀጥታ እና የመከላከያ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱን ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙ ሱዳናውያን በሙሉ ከእስር እንዲፈቱ ሃሳብ ማቅረቡ ነው የተገለጸው።

በዚህም 125 እስረኞች ከበርካታ ወራት የእስር ጊዜ በኋላ መፈታታቸውን ሱዳን ትሪቡን በዘገባው አመላክቷል፡፡

በሱዳን ከመፈንቅለ መንግስት በኋላ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለማርገብ በተወሰዱ እርምጃዎች እስካሁን ከ100 በላይ ሱዳናውያን ለህልፈት መዳረጋቸውን የሬውተርስ ሱዳን ትሪቡን ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.