Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል በቄለም ወለጋ ለሚገኙ በግጭት ለተፈናቀሉ ከ5 ሺህ በላይ ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በቄለም ወለጋ፣ ሃዋ ገላንና ስዮ ወረዳ ለሚገኙ በግጭት ለተፈናቀሉ 5 ሺህ 143 ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡

ድጋፉ በአማካይ በቤተሰብ 25 ኪሎ ግራም የስንዴ፣ 25 ኪሎ ግራም የባቄላ እና 5 ኪሎ ግራም የማሽላ ዘርን ያካተተ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የማዳበሪያና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን ለመግዛት የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግ መገለፁን ከዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ኮሙኒኬሽን ምክትል ሃላፊ አቶ ዘውዱ አያሌው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት ማብራሪያ፥ ተቋሙ በቀጣይ ለሚያደረገው የማደበሪያ እና የግብርና ግብአቶች ድጋፍ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.