Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውጤታማነቷን ለማሳደግ የውድድሮች አይነቶችን ማስፋት አለባት – አትሌት ፖል ቴርጋት 

 

አዲስ አበባ፣ግንቦት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ውጤታማነቷን ለማሳደግ የምትሳተፍባቸውን የውድድR አይነቶች ማስፋት አለባት ሲል ታዋቂው ኬንያዊ አትሌት ፖል ቴርጋት ተናገረ።

ከአትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ብርቱ ተፎካካሪዎች መካከል የነበረው ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት በሐዋሳ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ  በተዘጋጀው የኢትዮጵያ ወጣቶች የኦሊምፒክ ጨዋታዎች መክፈቻ  ስነ ስርዓት ተገኝቷል።

አትሌት ፖል ቴርጋት ከኢዜአ ጋር ባደረገው ቆይታ ቃለመጠይቅ ኢትዮጵያና  ኬንያ በረጅም ርቀት ሩጫ ከፍተኛ ስምና ዝና ካላቸው ሀገራት ከቀዳሚዎቹ  መሆናቸውን ጠቅሷል።

አሁን ላይ በአትሌቲክስ ስፖርት በረጅም ርቀት ሳይወሰኑ በሌሎች ርቀቶችና የሜዳ ላይ አትሌቲክስ ተግባራት በመሳተፍ ለውጤታማነት መትጋት አለባቸው ብሏል።

በኬንያ አዳዲስ የስፖርት አይነቶችን ለማስፋፋት  በዘርፉ ውጤታማ ከሆኑ ሀገራት ጋር ልምድና ተሞክሮ የመቅሰም ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽንም በተለያዩ የውድድር አይነቶች ስፖርተኞችን በሰፊው ለማፍራት የሚያስችሉ አማራጮች በመፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት አስረድቷል።

ይህን ለማድረግ ግን ቅድሚያ ለለውጥ ዝግጁ  መሆን ይገባል ያለው አትሌቱ በተለይ አዳዲስ ርቀቶችና የስፖርት አይነቶች ውጤታማ ለመሆን ጥሩ ተሞክሮ ካላቸው ሀገራት የጋራ ስምምነት በማድረግ መስራት  እንደሚቻል  አብራርቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.