Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የነበረው ለአዲስ ተሽከርካሪዎች ሠሌዳ የመሥጠት አገልግሎት ከሣምንት በኋላ ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥሬ ዕቃ ምክንያት ላለፉት ሦስት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ የመስጠት አገልግሎት ከአንድ ሣምንት በኋላ መሥጠት ይጀመራል ተባለ።

የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን አንባቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ በጥሬ ዕቃ ምክንያት እና በውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ላለፉት ሦስት ሣምንታት አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ መስጠት አልቻሉም፡፡

አሁን ላይ ግን የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ከጀርመን ሀገር ለማስመጣት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ አስታውቀዋል።

በርካታ ደንበኞች አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ለመውሰድ ተራ እየጠበቁ በመሆኑ በፍጥነት ተጨማሪ የማጓጓዣ ታሪፍ ተከፍሎ በአውሮፕላን እንዲመጣ ይደረጋልም ነው ያሉት።

አቶ ሰሎሞን አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ እየተጠባበቁ ላሉ ደበኞች ከአንድ ሣምንት በኋላ ማግኝት እንደሚችሉ ገልጸዋል።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.