Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ልማትና የሰብአዊ ድጋፍ አጠናክራ  ትቀጥላለች- የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ የአፍሪካ ዳይሬክተር

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ልማትና የሰብአዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ የአፍሪካ ዳይሬክተር ክሪስቲያን ዮካ ተናገሩ፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ከፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ የልዑካን ቡድን ጋር በኢኮኖሚያዊ ትብብር ጉዳዮች ላይ ተወያተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ በሀገር- በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የግሉን ዘርፍ በማጠናከር፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማ በማድረግና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ፈረንሳይ የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት አጋር መሆኗ እና በአሁኑ ወቅትም ከ11 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች በፈረንሳይ የገንዘብ ድጋፍ እየተከናወኑ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በኢንቨስትመንት፣ በስራ ፈጠራ፣ የግሉን ዘርፍ በማጠናከር ፣ በግጭት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋም፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ በሚያደርገው ጥረት÷ የፈረንሳይ መንግስትና የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ድጋፍ እንደሚያደርጉ  የኤጀንሲው ልዑክ መሪ ተናግረዋል፡፡

የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ የአፍሪካ ዳይሬክተርና የልዑኩ መሪ ክሪስቲያን ዮካ በኢትዮጵያ ውስጥ ወቅታዊና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ቢከሰትም÷ ሁለቱ ወዳጅ አገራት አብረው ከመስራት የሚያግዳቸው ነገር የለም ነው ያሉት፡፡

ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ልማትና የሰብአዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም የልዑካን ቡድን መሪው  ማረጋገጣቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከልዑካን ቡድኑ ጋር የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሄሌኔ ንጋርሚን ጋንጋ የተገኙ ሲሆን÷ ኤጀንሲው በፈረንጆቹ በ2023 እና 2024 በኢትዮጵያ ስለሚያከናውናቸው የልማት ድጋፎች ዕቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.