Fana: At a Speed of Life!

በውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው ውጤታማ ሥራዎችን ላከናወኑ ሴት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሴቶች ማኅበር በዲጂታል ሚዲያ ዘመን በውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው በርካታ ሥራዎችን ላከናወኑ ሴት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ  የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አለሚቱ ኡሙድ ባደረጉት ንግግር፥  ሴቶች በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎ እየተሻሻለ  መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ አሁንም  ቀሪ ሥራዎች እንደሚጠበቅበት አመላክተው÷ለዚህም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የመደገፍና የማበረታታት ግዴታውን እንደሚወጣ ነው የገለጹት፡፡

“ሴቶች በመገናኛ ብዙኃን ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበት እንሠራለን” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ የማህበሩ የቦርድ አባል  ጋዜጠኛ የሽዋ ማስረሻ ባስተላለፈችው መልዕክት÷ በመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ በርካታ ሥራዎችን ላከናወኑና ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አንጋፋ ሴት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም ማህበሩ አድሎኣዊ  የሆኑና ብልሹ አሰራሮችን በመታገል ጠንካራ ሴት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በመፍጠርና  አቅማቸውን በማጎልበት ረገድ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

በይስማው አደራው

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.