Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከሰኔ 2 ጀምሮ ለ6 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ለ6 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ከሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሊሰጥ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በጎንደር ከተማ ዛሬ በተሰጠው የሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና ፥ ሶስተኛ ዙር ክትባቱ ለ10 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥና እድሜያቸው 12 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ክትባት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቀቁን የክልሉ ጤና ቢሮ የክትባት አስተባባሪ አቶ ወርቅነህ ማሞ ገልጸዋል፡፡

አቶ ወርቅነህ አክለውም ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክልሎች በአማራ ክልል ደግሞ በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች እንደሚሰጥ ገልፀው ፥ ህብረተሰቡ በየአካባቢው በሚገኙ ጤና ድርጅቶችና በጊዜያዊ የክትባት ጣቢዎች በመገኘት እንዲከተብ ጥሪ አቅርበዋል።

በስልጠናው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሚዲያ ባለሙያዎችን ጨምሮ የአማራ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፣ ኢዜአ እና ከሌሎች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና አመራሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.