Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው አገር አቀፍ የከንቲባዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለሃብቶች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው አገር አቀፍ የከንቲባዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለሃብቶች የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

መድረኩ ከተሞች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች እንዴት መቋቋም እንዳለባቸው የመፍትሄ ሃሳብ ለመጠቆም እና በብቃት እና በስራ ፈጠራ አስተሳሰብ የተቃኘ አመራር እንዲኖር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።

የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ፕሬዚዳንት ኢንጅነር መላኩ እዘዘው÷ ምክክሩ በዕውቀት ፣ በመረጃ እና በልምድ የዳበረ አመራር ከግሉ ሴክተር ጋር በማስተሳሰር የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በስራ ፈጠራ በጥቃቅን አንስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከንግድ ልማት አንፃር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን ለማጠናከር እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

በአገራችን በየዓመቱ ሁለት ሚሊየን የሚሆኑ ወጣቶች አዲስ ስራ ፈላጊ መሆናቸውን የጠቆሙት ኢንጅነር መላኩ÷ ይህን ፍላጎት ለማጣጣም ጠንካራ ስርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በመድረኩ መክፈቻ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወሮ ጫልቱ ሰኒ እንደገለጹት÷ መንግስት የግሉ ሴክተር ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።

እስካሁንም የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ በመንደፍ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን÷ መድረኩ ለከተሞች አዲስ የስራ ዕድል ሃሳቦች በማፍለቅ ከተሞች በራሳቸው ገቢ እንዲተዳደሩ እና ባላቸው ጸጋ ልክ እንዲለሙ በማስቻል በኩል የላቁ ሃሳቦች የሚታዩበት ነው ብለዋል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ በበኩላቸው÷ የንግዱን የአሰራር በሂደትና የስራ አካበቢ ለነጋዴውም ሆነ ለሸማቹ የተመቻቸ እንዲሆን የፖሊሲ የስትራቴጂ እና የህግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን በመፈተሽ አዳዲሶቹን በመቅረፅ ነባሮችን በማሻሻል አየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በምክክሩ ከንቲባዎች ፣ በየከተማው የሚገኙ የንግድ እና ዘርፍ ምክር ቤት ማህበራት ተወካዩች፣ ከንግዱ ማህበረሰብ የተውጣጡ ግለሰቦች ስራ ፈጣሪዎች እና ምሁራን ተሳትፈዋል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.