Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ከሁለት ማኅበራት ጋር የማምረቻ ፋብሪካ መገንቢያ ቦታ የኪራይ ውል ሥምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሁለት ማኅበራት ጋር የማምረቻ ፋብሪካ መገንቢያ ቦታ የኪራይ ውል ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ”ከግሪንቢዝ ኢንቨስትመንት ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር” እና ”ከዳምቲት ቬት ፋርማ ትሬይኒንግ ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር ነው በቂሊንጦ ፋርማሲውቲካል ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የማምረቻ ፋብሪካ መገንቢያ የመሬት ኪራይ ውል ሥምምነት የተፈራረመው።

ቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ÷ ፋርማሲዩቲካል እና ባዮ ሜዲካል መሣሪያዎችን ለሚያመርቱ ፋብሪካዎች የተዘጋጀ ሙሉ መሠረተ ልማት የተሟላለት ፓርክ ነው።

ፋብሪካዎቻቸውን በፓርኩ ለመገንባት የመሬት ኪራይ ውል የፈጸሙት ማኅበራት በሚሰማሩበት ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡

“ግሪን ቢን ኢንቨስትመንት ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር” ÷ የአቮካዶ ዘይት እንዲሁም የሕክምና እና የውበት መጠበቂያዎችን የሚያመርት ሲሆን፣“ዳምቲት ቬት ፋርማ ትሬይኒንግ ኋላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ደግሞ ለሠብል አረም መከላከያ የሚሆኑ ኬሚካሎችን እንዲሁም የሰው፣ የእንስሳት እና የሰብል ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ የኬሚካል ምርቶችን የሚያመርት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በቆንጂት ዘውዴ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.