Fana: At a Speed of Life!

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሰባት የአፍሪካ ሀገራት መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሰባት የአፍሪካ ሀገራት መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ሰባት የአፍሪካ ሃገራት በበሽታው የተያዙና ሊኖርባቸው ይችላል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ሪፖርት ማድረጋቸውን አስታውቋል።
በዚህም ካሜሩን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ላይቤሪያ፣ ናይጄሪያ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ እና ሴራሊዮን ለድርጅቱ ሪፖርት ያደረጉ ሃገራት መሆናቸው ታውቋል።
በሀገራቱ በቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተጠርጥረው የተለዩ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 392 የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 44ቱ በሽታው እንዳለባቸው ተረጋግጧል።
የጤና ባለሙያዎች ሽፍታ፣ ትኩሳት፣ራስ ምታት፣ የጀርባ ህመም፣ የጡንቻ ህመም እና ድካም መሰል ምልክቶች የሚያሳዩ ህመምተኞችን በቅርበት ክትትል እንዲያደርጉ ድርጅቱ ማሳሰቡን አናዶሉ በዘገባው አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.