Fana: At a Speed of Life!

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት የጀመረውን ሰላም የማረጋገጥ ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል- ሜ/ጀ ከፍያለው አምዴ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት የጀመረውን ሰላም የማረጋገጥ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አዲሱ የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው አምዴ ገለጹ፡፡
ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው አምዴ አዲሱ የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ መሆናቸውን ተከትሎ በግልገል በለስ ከተማ የትውውቅና የርክክብ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ሜጀር ጀኔራል ከፍያለው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ኃይል አዛዥና የበላይ ጠባቂ በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ጀኔራል መኮንኑ አሁን ላይ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ከመላው የኮማንድ ፖስቱ አመራርና አባላት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚወጡ ነው የተናገሩት።
ፀረ ሰላም ኃይሎችን መመንጠር፣ የህዳሴ ግድቡን ስራ ያለምንም የፀጥታ ችግር ማስቀጠል፣ በዞኑ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን መመለስ እና ሚሊሻዎችን በየአካባቢው ማደራጀት የኮማንድ ፖስቱ ተልዕኮ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ጀኔራል መኮንኑ በባለፉት ሶስት ወራት ወስጥ የፀጥታ ኃይሉ በጥምረት በፈፀመው ግዳጅ በመተከል ዞን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ፀረ ሰላም ኃይሎች ላይ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን እና በጠላት እጅ የነበሩ ቀበሌዎችን ነፃ በማውጣት አንፃራዊ ሰላም ማስፈን ተችሏል ብለዋል።
ቀደም ሲል የተቀናጀ ኮማንድ ፖስቱን በበላይነት ሲመሩ የነበሩት ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ÷ ጥምር የፀጥታ ሃይሉ ባሳደረው ጫና ከ1 ሺህ 700 በላይ ህገወጥ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን በማስረከብ ጭምር በሰላም ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀላቸውን አስታውሰዋል።
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የየወረዳው አመራሮች የመከላከያ ሰራዊቱ እና የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም በቀጠናው የተሰማሩ የክልል ልዩ ኃይል አመራሮች መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
82
Engagements
Boost post
75
3 Comments
4 Shares
Like

Comment
Share

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.