Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከዑራኤል እስከ ፑሽኪን አደባባይ የሚከናወነውን የመንገድ ዳር ማስዋብ ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከዑራኤል እስከ ፑሽኪን አደባባይ ያለውን መንገድ በአረንጓዴ የማስዋብ ስራ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች ፕሮጀክቱ በ60 ቀናት ከሚተገበሩ ሰው ተኮር ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተናግረዋል፡፡
መሰል ተግባራት ከተማዋን በማስዋብና የዜጎችን አኗኗር በመቀየር ረገድ አስተዋጿቸው ከፍተኛ በመሆኑ በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች በስፋት እየተሰሩ ነው ብለዋል።
ዜጎች በንፁህና አረንጓዴ ስፍራ የመኖር መብት እንዳላቸው የተናገሩት ከንቲባዋ÷ የከተማ አስተዳደሩም የነዋሪዎቹን ፍላጎት ለማሟላት በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሆነ መግለጻቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አዲስ አበባን እንደስሟ አዲስ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት መላው የከተማዋ ነዋሪ፣ ባለሃብቶችና በጎ ፍቃደኞች ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም የበኩላቸውን አሻራ እንዲያስቀጡ ከንቲባ አዳነች ጥሪ አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.