Fana: At a Speed of Life!

በሱሉልታ በዛሬው ዕለት በደረሱ ሁለት የእሳት አደጋዎች በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱሉልታከተማ በዛሬው ዕለት ሁለት ጊዜ በደረሱ የእሳት አደጋዎች በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡
የከተማዋ ማዘጋጃ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጄ ያኢ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ አደጋው ዛሬ ንጋት 10፡00 እና ከሰዓት 7፡00 ሰዓት ላይ በ01 ቀበሌ ባጃጅ ተራ አካባቢ ተከስቷል፡፡
በአደጋውም የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች፣ መኖሪያ ቤቶች እና መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ንጋት 10፡00 አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤ ከጭነት ተሽከርካሪ የተነሳ እሳት መሆኑን የገለጹት አቶ ደረጄ፥ ከቀኑ 7፡00 አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤ ደግሞ እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አደጋው ያደረሰው የጉዳት መጠን በመጣራት ላይ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
አደጋዎቹ በከተማዋ ነዋሪዎች እና በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያዎች ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡
በከተማዋ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም በደረሰ የእሳት አደጋ በሆቴሎች እና በንግድ ድርጅቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.