Fana: At a Speed of Life!

በባንኮች የደንበኞች የቁጠባ ሂሳብ መጠን 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባንኮች የደንበኞች የቁጠባ ሂሳብ መጠን 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው የዜጎች የቁጠባ ባሕል በሚፈለገው ደረጃ ላይ ደርሷል ባይባልም በእጅጉ እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመው÷ እስከ መጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ድረስ በባንኮች የደንበኞች የቁጠባ ሂሳብ መጠን 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር መድረሱን ተናግረዋል።
አጠቃላይ ባንኮች የሰጡት የብድር መጠን 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ሲሆን÷ የተበዳሪዎች ቁጥርም ከ350 ሺህ አልፏል ብለዋል፡፡
የባንኮች የቅርንጫፍ ብዛት፣ የሚሰጡት የብድርና ቁጠባ አገልግሎት፣ የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ማዋል ለባንኮች ተደራሽነት መጨመር ምክንያት መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ከቁጠባ ተደራሽነት አንጻር የተሻለ ቢሆንም÷ የብድር ተደራሽነቱ ግን በአብዛኛው ለትላልቅ ተበዳሪዎች የተሰጠ በመሆኑ ውስንነት ያለበት መሆኑን አስረድተዋል።
በተለይም በእርሻ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰጠው ብድር ዝቅተኛ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ይሻል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ንግድ ባንክ በመንግስት ቅድሚያ የተሰጣቸውን ዘርፎች በመደገፍ እየሰሩ እንደሚገኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የግል ባንኮችም በአገሪቱ የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎችን እየደገፉ መሆኑን ገልጸው÷ በግል ባንኮች በቂ የገንዘብ ክምችት አለመኖርና የብድር ስጋት መጨመር ለብድር ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆን በምክንያትነት አንስተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.