Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የ6ኛ ዙር ተመራጭ ሴቶች ኮከስ የምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት የ6ኛ ዙር ተመራጭ ሴቶች ኮከስ የምስረታ ጉባኤ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በኮከስ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ ፥ ኮከሱ በየአምስት ዓመቱ አዲስ ምክር ቤት ሲቋቋም አብሮ የሚመሰረት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ዓላማውም የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ፣ መብትና ጥቅም ማስከበር እንደሆነ መግለጻቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሁሉም ዘርፎች የሴቶችን ተሳትፎ ፍትሃዊነት እንዲኖረው ከማድረግ አንፃር ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልጸው ፥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሣትፎና ተጠቃሚነትን በተሟላና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ ኮከሱ ጠንክሮ እንዲሰራም አሳስበዋል፡፡

የኢፌዴሪ ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ ወይዘሮ ኪኒያ ጁነዲን በበኩላቸው÷ የደቡብ ክልል የፍቅር፣ የሠላም፣ የአብሮነትና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኑን አውስተዋል፡፡

የክልል ምክር ቤት ተመራጭ የሴት ኮከስ አባላት ተደራራቢ ኃላፊነት እንዳለባቸው አውቀው ለሴቶች ሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ ተግተው እንዲሰሩ ም ሰብሳቢዋ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.