Fana: At a Speed of Life!

ዩ ኤስ ኤይ ድ ከ200 በላይ መስማት ለተሳናቸው ሴቶች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በአዲስ አበባ ከ200 በላይ መስማት ለተሳናቸው ሴቶች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰንና የዩ ኤስ ኤይ ድ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ፕሮጀክቱን ይፋ አድርገዋል።

ለ3 ዓመት በሚቆየው ፕሮጀክት ‘ተኪ’ የወረቀት ቦርሳ አምራች ድርጅት ከአሜሪካ በሚያገኘው የ550 ሺህ ዶላር ድጋፍ ከአዲስ አበባ ከተማ፣ ከአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽንና ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር የፕላስቲክ ቦርሳዎችን በማምረትና በማሰራጨት ለ200 መስማት ለተሳናቸው ሴቶች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

የተራድኦ ድርጅቱ  ከ‘ተኪ’ የወረቀት ቦርሳ አምራች ድርጅት ጋር ያለው ትብብር አሜሪካ በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች አካታችነት፣ የአካባቢ ጥበቃና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ተብሏል።

‘ተኪ’ እስካሁን ከ1 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ የወረቀት ቦርሳዎች ማምረት መቻሉን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በፈረንጆቹ 2021 ለኢትዮጵያ ከ1 ጥብ 2 ቢሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.