Fana: At a Speed of Life!

በባሕር ዳር እየተካሄደ ባለው ሕግ የማስከበር ሥራ 223 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው ሕግ የማስከበር ሥራ 223 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ እንደገለጹት÷ የህብረተሰቡን ሕግ ይከበርልን ጥያቄ ያዳመጠው መንግስት ለሕዝቡ በገባው ቃል መሰረት ሕግ የማስከበር ስራ አጠናክሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እስካሁን ድረስም በባሕርዳር ከተማ በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 223 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የገለጹት።
አስተዳደሩ ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸው÷ በከተማዋ ውስጥ ከ2 ሺህ በላይ በሕገ ወጥነት የተያዙ ኮንቲነሮች እና ሼዶች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡
ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር ተመጋጋቢና ተጨማሪ ውበት መስጠት የሚችሉ ኮንቴነሮችንና ሼዶችን በመገንባት ለከተማችን ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
በሕገ ወጥነት ለማህበራት በተዘጋጀ ቦታ ላይ ከ1 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑ ሕገ ወጥ ቤቶችን በማፍረስም ለበርካታ ዓመታት የቆየ የመልካም አስተዳደር ችግር ተፈትቷል ነው ያሉት፡፡
በርካታ ሕገ ወጥ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ሥር አውለናል ማለታቸውንም ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሕግና ስርዓት ለማስፈን በሚያደረግው ጥረት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠትና ሕገ ወጦችን በማጋለጥ እያደረገ ያለው ትብብር መልካም የሚባል በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.