Fana: At a Speed of Life!

የፊታችን ዕሁድ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህግ ማስከበር ፣ በህልውና እና በህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻዎች ወቅት ጀግንነት ለፈፀሙና የላቀ የስራ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር የፊታችን እሁድ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የከተማዋ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በመሆኑም ስነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦

በዚህም ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር (ኦሎፒያ አደባባይ) ፣ ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ በላይና በታች፣ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ፣ ከቸርችል ጎዳና በሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፖስታ ቤት ፣ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፣ ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር ለተሸከርካሪዎቸ ዝግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና አካባቢ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር ፣ ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሜክሲኮ አደባባይ ፣ ከሚክሲኮ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር መብራት ፣ ከሰንጋ ተራ በቴሌ ባር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች በድሉ ህንፃ አካባቢ፣ ከንግድ ማተሚያ ቤት በውስጥ ለውስጥ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦርማ ጋራዥ አካባቢ ፣ ከሸራተን ወደ አምባሳደር ለሚመጡ ፍል ውሃ አካባቢ ፣ ከካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10 ሰዓት 30 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት መሰረት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.