Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ህዝቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች ከመመለስ አንፃር አመራሩ ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባው የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የተቋቋሙ የተለያዩ ግብረሃይሎች መካከል ክላስተር በ90 ቀናት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል፡፡

በዚህም የክልሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ቢሮ ሃላፊ አቶ አዩብ አህመድ ፍትና ፀጥታን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት÷ ህዝቡ በትራንስፖርት ላይ የሚያነሳቸውን ጥያቄ ለመመለስ በተከናወነ ተግባር የትራፊክ ደንብ በተላለፉ 3 ሺህ 872 ተሸከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል፡፡

በትራንስፖርት ላይ የሚፈፀሙ ስርቆት ለመቆጣጠርና ለመከላከል በተከናወነ ስራም 55 ተሸከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው 28ኙ ለህግ ቀርበዋል ብለዋል፡፡

በትራፊክ ፖሊሶች አባላት ላይ የሚስተዋሉ የስነ ምግባር ችግር ለመቅረፍ በተደረገ ክትትልና ምርመራ 16 አባላት ማለየታቸውንና እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በወንጀል የተሳተፉ በ4 የፖሊስ አባላት ምርመራ ተደርጎ ክስ መከፈቱንና በቀጣይም የፖሊስ አባላትንና ሚሊሻ አባላትን የማጥራት ስራም በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከህገወጥ የነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ 4 ማደያዎች መታሸጋቸውን እና 900 ሊትር እንዲሁም 8 በርሜን ቤንዚል በቁጥጥር ስር መዋሉን ነው የተናገሩት፡፡

በሌላ በኩል 200 ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታ በላይ እርምጃ መወሰዱንና በ40 ገለሰቦች ላይ ክስ መከፈቱን መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ካሊድ አብዲ ከኢኮኖሚ ጋር በተያያዘ ባቀረቡት ሪፖርት ÷ በክልሉ በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በአግባቡ ለህዝቡ እየተሰራ መሆኑን እና የኑሮ ውድነት እንዲባባስ በሚያደርጉ አካላትን ከመቆጣጠር አንፃር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

በክልሉ ተጨማሪ በ3 ስፍራዎች ላይ የቅዳሜ ገበያ ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ቢሆንም ከአቅርቦት ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች እንደሚስተዋል ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እንደተናገሩት ከወራት በፊት የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኝነት እየተሰራ የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት መቀዛቀዝ ይታያል፤ስለሆነም አመራሩ ህዝቡ ጥያቄ ከመመለስ አንፃር ሀላፊነቱን በአግባቡ መወጣት አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.