Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በጅማ ከተማ የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።

አደጋው በጅማ ከተማ በቾ ቦሬ ቀበሌ ከምሽቱ 2:20 ሰዓት የደረሰ ሲሆን፥ በመኖሪያ ቤቶችና ግቢ ውስጥ በነበረ ተሽከርካሪና ባጃጆች ላይ ጉዳት አድርሷል።

አደጋው ከአንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ በከተማው ነዋሪዎች፣ በእሳት መከላከል ቡድንና በፀጥታ ሃይሎች ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የከተማው ፖሊስ የአደጋ መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ገልፆ፥ አደጋውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ርብርብ ላደረጉ የከተማው ነዋሪዎችና ሌሎች አካላት ምስጋና አቅርቧል።

 

በሙክታር ጠሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.