Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ሠመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣  2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አፋር ሠመራ ገቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሠመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአፋር ክልል በሚኖራቸው ቆይታ ከክልሉ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.