Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሚላኩ ሰብዓዊ እርዳታዎች ለማሳለጥ እያደረገ ከሚገኘው ሁሉን አቀፍ ጥረት በተጓዳኝ አሸባሪው ህወሓት ለጥፋት ዓላማው ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳይተላለፉ በትኩረት እንዲሠራ አሳስበዋል።

በሽብር ቡድኑ ህወሓት ወረራ ምክንያት የአፋር ህዝብ ከ1 ሚሊየን በላይ የሚሆን ተፈናቃዮችን ይዞ መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ የሚገኘውን ጥረት ተፈጻሚነት ያሳየው ቀናት ትብብር የሚደነቅ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ለዚህም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች የማህበረሰብ መሪዎች እንዲሁም የክልሉ ነዋሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል ነው ያሉት፡፡

መንግስት በተለያዩ ክልሎች በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ከተያዩ ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለመደገፍ በትኩረት አየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ከዚ ህውስጥም ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሚደረገው ድጋፍ አንዱ መሆኑን ገልጸው÷ ለተገጂዎች ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን የበለጠ ለማሳለጥ ከዓለም ምግብ ድርጅትና ሌሎች አጋሮች ጋር በቅንጅት አየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የሰብዓዊ እርዳታው በቀን እስከ 200 ኮንቮይ ተሽከርካሪ በሰርዶ ኬላ ተገቢው የፍተሻና ተያያዥ ቁጥጥር ከተደረገበት በኋላ አንደሚላክ በጉብኝታቸው መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይሁንና በተደረገዉ ፍተሻ ለሽብር ቡድኑ የጥፋት አላማ ማስፈጸሚያ ሊውሉ የሚችሉ ከተፈቀደው የነዳጅ መጠን በላይ ተጨማሪ ነዳጅና አንዳንድ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ለማሳለፍ ሙከራዎች አንዳሉ መገንዘባቸውን  ነው የተናገሩት፡፡

መሰል ተግባራት ከሰብዓዊ አቅርቦት ህጉ የሚጣረሱ በመሆኑ ከሚመለከታቸው ሰብዓዊ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር መንግስት አንደሚነጋገርበት ያስገነዘቡት አቶ ደመቀ÷በአጠቃላይ መንግስት ሰብዓዊ እርዳታውን ለማሳለጥ ከሚያደረዉ ሁሉን አቀፍ ጥረቶች ጉን ለጎን ጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ላይ ተገቢውን የቁጥጥርና ክትትል ስራቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

መንግስት ለትግራይ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እያደረገ የሚገኘውን ጥረት በመደገፍ እያሳየ ያለው ቀናንትና ትብብር የሚደነቅ ነው ብለዋል አቶ ደመቀ።

መንግስት በተለያዩ ክልሎች በሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት የተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር በመሆን ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች ‘ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ’ አቅርቦትን የበለጠ ለማሳለጥ ከዓለም ምግብ ፕሮግራምና ከሌሎች አጋሮች ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.