Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በመዲናዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች የቤት ግንባታ የሚውል የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ግንባታ የሚውል 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፉ ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን በሁለንተናዊ መልኩ ለማዘመን እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የተበረከተ ስጦታ መሆኑን ኮሚሽነር ደበሌ ተናግረዋል፡፡
 
ኮሚሽኑ ቤቶቹ እስኪጠናቀቁ ድረስ በቅርበት ክትትል እንደሚያደርግ የጠቆሙት ኮሚሽነሩ÷ተሰርተው ሲጠናቀቁም ለነዋሪዎቹ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው÷ ከተማ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የሆኑ እና መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጡ በርካታ ፕሮጀክቶችን እውን እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የጉምሩክ ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ ለከተማ አስተዳደሩ እደረገ ስላለው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኮሚሽኑ ባደረገው ድጋፍ 27 አባዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 35 ቤቶች እንደሚገነቡም በግንባታበግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.