Fana: At a Speed of Life!

አርጀንቲናዊው ኮከብ ካርሎስ ቴቬዝ ከእግር ኳስ ዓለም መገለሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው የእግር ኳስ ኮከብ ካርሎስ ቴቬዝ ከእግር ዓለም መገለሉን ይፋ አደረገ።

የቀድሞው የማንቼስተር ዩናይትድ፣ ማንቼስተር ሲቲ እና ጁቬንቱስ ኮከብ በ38 አመቱ እግር ኳስ ማቆሙን በይፋ አስታውቋል።

“በአወዛጋቢ” የእግር ኳስ ህይወቱ የሚታወቀው ቴቬዝ አሳዳጊ አባቱን ባለፈው አመት በኮቪድ ሳቢያ ማጣቱ ይታወሳል።

አሳዳጊ አባቱን በሞት ካጣ በኋላ ሁሉም ነገር አስቸጋሪ እንደሆነበትም ተናግሯል።

ቴቬዝ በቦካ ጁኒየርስ፣ ኮረንቲያስ፣ ዌስትሃም፣ ማንቼስተር ዩናይትድ፣ ማንቼስተር ሲቲ፣ ጁቬንቱስ እና ሻንጋይ ሸኑአ ተጫውቶ አሳልፏል።

በክለብ ቆይታውም የሃገር ውስጥ ሊግ ውድድርን ጨምሮ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አግኝቷል።

የእግር ኳስ ህይወቱን አሐዱ ባለበት ቦካ ጁኒየርስም ጫማውን ሰቅሏል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.