Fana: At a Speed of Life!

የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች መለያ ስቲከር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚገልፅ መለያ ይፋ ሆነ፡፡
መለያው ሁለት አይነት ሲሆን÷ ለመደበኛ ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እና በክልል ለሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡
መለያው ተሽከርካሪዎቹ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን ለነዳጅ ማደያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት መረጃ የሚሰጥም ነው፡፡
በዚህም ሙሉ ሰማያዊ ቀለም ያለው መለያ ለሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች የሚያገለግል ሲሆን÷ በነጭ መደብ የተዘጋጀው መለያ ደግሞ በክልል ለሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎ ሰጪ ተሽከርካሪዎች የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡
በቅርቡ ተግባራዊ ለመሆን በዝግጅት ላይ የሚገኘው የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ተጠቃሚ የሚሆኑ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሽከርካሪዎችን የመለየትና መረጃ የማጥራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.