Fana: At a Speed of Life!

ከመኸር ሰብል በአገር አቀፍ ደረጃ ከ336 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመኸር ወቅት ሰብል በአገር አቀፍ ደረጃ 336 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ፥ በመኸር ወቅት 13 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 12 ነጥብ 8 ሚሊየን (97 በመቶ) በዘር መሸፈኑን ገልጿል፡፡

በዚህም 374 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ 336 ነጥብ 60 ሚሊየን (90 በመቶ) ኩንታል ምርት መሰብሰብ ተችሏል ብሏል።

ይህ አፈጻጸም በመሬት ሽፋን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በዘር ከተሸፈነው 13 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር ጋር ሲነጻጸር የ500 ሺህ ሄክታር መቀነስ እንደሚያሳይ ነው የተጠቆመው፡፡

በምርት ደግሞ አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 341 ሚሊየን ኩንታል፥ በ5 ሚሊየን ኩንታል ያነሰ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ይህም የሆነው በግጭት ምክንያት ማምረት ያልቻሉ ዞኖች እና በትግራይ ክልል ላይ ያለው ሪፖርት ባለመካተቱ እንደሆነ መመላከቱን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.