Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በሶማሌ ክልል ለ1 ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት በሶማሌ ክልል ቱሊጉሌድ ወረዳ ለ1 ሺህ አባወራዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ የበቆሎንና የማሽላ ዘርን የሚያካትት ሲሆን÷ በክልሉ ላሉ 4 ሺህ አባወራዎችም የስንዴ ስርጭት በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በቄለም ወለጋ፣ ሃዋ ገላን እና ስዮ ወረዳ ለሚገኙ በግጭት ለተጎዱ 5 ሺህ 143 ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ድጋፉ በአማካይ በቤተሰብ 25 ኪሎ ግራም የስንዴ፣ 25 ኪሎ ግራም የባቄላ እና 5 ኪሎ ግራም የማሽላ ዘርን ያካተተ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.