Fana: At a Speed of Life!

977 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) 977 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ 977 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡

ከተመለሱት ውስጥ ስድስት ህጻናት የሚገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ 971 ዜጎች ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ33 ሺህ 298 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.