Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር  አጎስቲኖ ፓልሴ ጋር የተፈናቀሉ ወገኖችን መረዳት በሚቻልበት ሁኔታ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ የጣሊያን ኤምባሲ ካውንስለር አሪያና ካታላኖ፣ የፖለቲካ ዘርፍ  ኃላፊ እና     የጣሊያን የልማት ትብብር  ኃላፊዋ ተገኝተዋል።

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ባካሄደው ወረራ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ስለሚረዱበት ሁኔታ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን ከአፋር ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደር አጎስቲኖ እና ባልደረቦቻቸው÷ የጣሊያን መንግስት ህወሓት በአፋር ህዝብ ላይ ስላደረሰው ጉዳት አስመልክቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የማሳወቅ ስራ መስራቱን ጠቁመዋል።

የጣሊያን የልማት ትብብር ኃላፊዋ ኢሳቤላ ሉሳፌሪ በበኩላቸው÷ እሳቸው የሚመሩት የተራድኦ ድርጅት በአፋር ክልል እየተተገበረ ያለውን የልማት ስራ ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.