Fana: At a Speed of Life!

የወባ ወረርሽኝ እየጨመረ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወባ ወረርሽኝ እየጨመረ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ጋር በመሆን በወባ ወረርሽኝ፣ በኮሮና ቫይረስና እና የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ÷የወባ ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ በህብረተሰቡ ዘንድ መዘናጋት እየተስተዋለ ነው፡፡

ባለፉት አራት ወራትም በተለይ በደቡብ ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ወረርሽኙ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

አጎበር በአግባቡ አለመጠቀም፣ የአመራሩና ህብረተሰቡ መዘናጋት፣ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የነበረው የጸጥታ ችግር ለወረርሽኙ መስፋፋት በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪ ድርቁን ተከትሎ የተከሰተው ከባድ ዝናብ ለወባ ወረርሽኝ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወርሽኙን ለመግታትም ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ፥ ኀብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ መከሰቱን የሚያሳይ መረጃ እንዳልተገም ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹ ሲሆን ፥ ሆኖም ቅድመ ጥንቃቄዎች እየተደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.