Fana: At a Speed of Life!

ሁለቱ ክልሎች በአዋሳኝ ድንበሮች ላይ የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልና የጋምቤላ  ክልል  መንግስታት በአዋሳኝ ድንበሮች ላይ የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ውይይት አድርገዋል።

የሁለቱ ክልሎች የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች በተገኙበት በድንበሮች አካባቢ የሚከሰተውን ግጭት ለማስቆም በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ  ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በዲማ ከተማ በተደረገው ውይይት፥  በሱርማ  እና በአኘዋክ  ብሄረሰቦች መካከል የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት አመራሮች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በውይይቱ የአኝዋክ ዞን አስተዳደር፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የድማ፣ የሱርማ የቤሮ ወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የሚልሻ ጽ/ቤት፣የፓሊስ፣ የልዩ ኃይል ፣ የፌደራል ፓሊስና የሀገር መከላከያ አመራሮች መገኘታቸውን ከጋምቤላ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.