Fana: At a Speed of Life!

ባለሥልጣኑ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ ተቋም እንደሌለ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ ተቋም አለመኖሩን የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን አስታወቀ ፡፡
ባለሥልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መቋቋም የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እና በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 መሰረት ከፌደራል ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ስያሜ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም እንደተቋቋመ የሚገልጽ መልዕክት በማህበራዊ ድህረ-ገጽ እየተዋወቀ እንደሚገኝ ነው ባለስልጣኑ የጠቆመው፡፡
“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በማለት እራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘው ይህ ተቋም ከባለሥልጣኑ ምንም አይነት ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ስለሆነም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል፡፡
በቀጣይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ መገለጹንም ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.