Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በኢንቨስትመትና ሌሎች ተያያዠ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የሚመራ ልዑክ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በኢንቨስትመትና ሌሎች ተያያዠ ጉዳዮች ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ ተወያይተዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት÷ የቱርክ ባለሃብቶች በክልሉ በኢንቨስትመንትና በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ እየተሳተፉ ነው።

የዓባይ ድልድይ ግንባታ ላይ በማማከር፣ በምስራቅ አማራ እየተገነባ ባለው የባቡር መንገድ በተቋራጭነትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል በእርሻ፣ በማዕድን፣ በጨርቃጨርቅ፣ በቱሪዝምና ሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች እምቅ ሃብት ያለው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

ቱርክ በፊልም፣ በሙዚቃና ሌሎች የባህል ልማቶች ሰፊ ልምድ ያላት አገር በመሆኗ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማሳደግ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል ተናግረዋል።

የቱርክ ባለሃብቶች ያላቸውን እውቀት፣ ልምድና ክህሎት ተጠቅመው ወደ ክልሉ ኢንቨስት ለማድረግ ቢመጡ የክልሉ መንግስት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ በበኩላቸው÷ በርካታ ባለሃብቶች በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በጨርቃ ጨርቅ፣ በጥጥ ልማት፣ በመሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎች ዘርፎች በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በቀጣይም አሁን ያለውን መልካም የግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንሰራለን ሲሉ አምባሳደሯ አስረድተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.