Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ወደ ትግራይ ክልል በወጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ ያለበትን ሁኔታ አደነቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ትግራይ ክልል በወጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እየቀረበ ያለበትን ሁኔታ አደነቀች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፥ በአጠቃላይ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ወጥ በሆነ መንገድ የቀጠለው የሰብዓዊ እርዳታ እቅቦትን እንደምታደንቅ አስታውቋል።

ባለፉት ሰባት ቀናት 1 ሺህ 100 ተሽከርካሪዎች የነብስ አድን እና የተመጣጠነ ምግብ፣ የህክምና ቁሳቁሶችን እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ይዘው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን ጠቅሷል።

የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የፌደራል መንግስት እና የክልለ መንግስታት እያደረጉት ያለውን ቅንጅትንም እንደምታደንቅ ነው ያስታወቀችው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች ጥረትም የሚደነቅ መሆኑን ጠቁሟል።

ይህን አጋጣሚንም ሁሉም ወገኖች ግጭትን በዘላቂነት ለማቆም እንዲጠቀሙበት ነው መግለጫው የጠየቀው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.