Fana: At a Speed of Life!

በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን ቱርክ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት ቱርክ ገብቷል፡፡
 
ልዑካኑ የቱርክ መንግስት ባዘጋጀው ኢ ኤፍ ኢ ኤስ 2022 በተሰኘው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ ነው ቱርክ የገቡት፡፡
 
ከዝግጅቱ ጎን ለጎን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጄነራል ያሳር ጉለር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም በአቅም ግንባታና ወታደራዊ ድጋፎች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በቱርክ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.