Fana: At a Speed of Life!

ስለድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የውሃ ሀብት ግንዛቤ ለመፍጠር በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና ውሃ ሀብት ጋር በተያያዘ ሰፊ ግንዛቤ ለመፍጠር በቅንጅት መሥራት አስፈላጊ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተርር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ተናገሩ።

የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መማክርት ፎረም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ በውሃና- ውሃ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ምሁራንና መገናኛ ብዙኀንን በማቀናጀት የተገኘውን ውጤት ከፍ ለማድረግና ሀገሪቱን ለማሻገር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መገናኛ ብዙኀን ታላቁ ሕዳሴ ግድብን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ውሃ ሀብትንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞችን ትኩረት ያደረጉ በሀገር ውስጥና በውጪ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን በቋሚነት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ስለ ውሃ ሀብት ሕጻናትን ጭምር ለማስገንዘብ መሠራት እንዳለበት ሚኒስትሩ ጠቅሰው ለዚህም ይህ ፎረም ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

ፎረሙ በውሃና- ውሃ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ምሁራንና መገናኛ ብዙኀን አንድ ላይ በማምጣት ቅንጅት ፈጥረው የሚሠሩበትን መድረክ ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል።
በመድረኩ ሦስት ሰነዶች የሚቀርቡ ሲሆን በቀረቡት ሰነዶችና በቀጣይ የፎረሙ አቅጣጫ ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል ፡፡

ፎረሙ ምህራንን፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎችን፣ የመገናኛ ብዙኀንን አንድ ላይ በማምጣት በውሃ ሀብት ዙሪያ በጋራ የሚሠሩበት መድረክ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.