Fana: At a Speed of Life!

የነዋሪዎችን የቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮች እየተፈለጉ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዋሪዎችን የቤት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን እያፈላለገ እንደሆነ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የከተማ እና መሠረተ-ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ2014 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡
በዚህ ወቅትም ሚኒስቴሩ የቤት ችግርን ለመቅረፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተለያዩ አማራጮችን እያፈላለገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በተለይም ለግሉ ሴክተር ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ የግሉ ሴክተር እየገነባ፣ የራሱን ድርሻ እየወሰደ፣ ዜጎችን የቤት ባለቤት እንዲያደርግ ስትራቴጂ መቀየሱን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
ቤቶች ሲገነቡ የሚያስፈልጉትን መሠረተ-ልማቶች ጭምር ለመገንባት መንግስት የአስቻይ ሚናውን ለመወጣት እየጣረ ይገኛልም ነው ያሉት ሚኒስትሯ።
ከጦርነቱ በኋላ የተጎዱ ከተሞችን መልሶ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የጋሸና እና የኮምቦልቻ መንገዶች ጥገና ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ሆኖም ግን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ሚኒስትሯ መናገራቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.