Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ደንቡን በአብላጫ ድምጽ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት “ልጆቻችንን ለመጠበቅ የወጣ ደንብ” በሚል የተዘጋጀውን ዝርዝር የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ በአብልጫ ድምፅ አሳልፏል፡፡

በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ አምሥት “ሪፐብሊካን” የቀረበውን ዝርዝር ደንብ ሲደግፉ ሁለት “ዴሞክራቶች” ደግሞ መቃወማቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ይሁን እንጀ ረቂቅ ደንቡ ህግ ሆኖ ይጸድቅ ዘንድ በሴኔቱ ተቀባይነት ማግኘትና መፅደቅ ይኖርበታል።

ረቂቁ ሰዎች መሣሪያ መግዛት የሚችሉበትን ዕድሜ ከ18 ወደ 21 ከፍ እንዲል ይደነግጋል።

መሣሪያ እንዲገዛ ዕድሜው የሚፈቅድለት ማንኛውም ሰው ከ15 ተተኳሽ ጥይቶች በላይ የሚይዝ የጥይት መጋዘን መግዛት እንደማይችልም በወጣው ደንብ ተደንግጓል፡፡

ማንኛውም መሣሪያ የታጠቀ ሰው ቤተሰብ ፣ ፖሊስ እና ሌላ አካል ÷ ግለሰቡ የአዕምሮ መታወክ ደርሶበታል ፣ ወይም ሌሎችን የመጉዳት አደገኛ አዝማሚያ ይስተዋልበታል ብለው ሲጠራጠሩ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ መሣሪያ የመጠቀም መብቱን እንዲነሳ የመጠየቅ መብት የሚፈቅደው ደንብ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ በቀጣይ ለውሳኔ እንደሚቀርብ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ በአሜሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ከመሣሪያ ጋር በተያያዙ ግጭቶች መቀጠፉን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.