Fana: At a Speed of Life!

ህብረተሰቡንና የጸጥታ አካላትን በማቀናጀት አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን እንከላከላለን – ዶ/ር ቀነአ ያደታ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡንና የጸጥታ አካላትን በማቀናጀት አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን ለመከላከል እንሰራለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነአ ያደታ ገለጹ፡፡

ቢሮው ባዘጋጀው የሰላምና ጸጥታ ግንባታ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና የሰላም ሰራዊት ደንብ ረቂቅ ላይ ዛሬ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል።

የምክክር መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቀነአ ያደታ ፥ ረቂቅ ደንቡ የተጀመረውን የከተማዋን ሰላም የማሳለጥ ስልት ያለው በመሆኑ በጸጥታ ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅት ያጠናክራል ብለዋል።

የህዝባዊ ሰራዊት በጎ ስራዎችን በመመሪያና በፖሊሲ በመደገፍ ተቋማዊ እንዲሆን ያስችላል ያሉት ኃላፊው፥ ረቂቅ ደንቡ በከተማዋ የሚታየውን የጽንፈኝነት አስተሳሰብ ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነም አመላክተዋል፡፡

ህብረተሰቡንና የጸጥታ አካላትን በጋራ በማቀናጀት የመዲናዋን ሰላም ከማስጠበቅ ባለፈ አክራሪነትንና ጽንፈኝነትን ለመከላከል ይሰራል ነው ያሉት የቢሮ ኃላፊው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ በበኩላቸው፥ በህብረተሰቡና በጸጥታ አካላት መካከል በቅንጅት የሚሰሩ የሰላም ስራዎች በፖሊሲና በስትራቴጂ መመራት አለባቸው ብለዋል።

በከተማ አሰተዳደሩ የሚቋቋመው የሰላምና ጸጥታ መዋቅር የመዲናዋን የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መቀመጫነት ያገናዘበ መሆን እንዳለበትም ነው ያብራሩት።

በምክክር መድረኩ ላይ ምሁራን፣ ከፌደራልና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ ባለድርሻ አካላትና የቀድሞ ሰራዊት አባላት ተሳትፈዋል።

በምክክሩ የሚገኙ ግብዓቶችን በመሰብሰብ በረቂቅ ደንቡ ላይ እንደሚካተት መገለጹንም ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.