Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል 4 ሺህ 155 ሕገ ወጥ የሠራተኞች ቅጥር ተሰረዘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል 4 ሺህ 155 ሕገ ወጥ የሠራተኛ ቅጥር፣ ዝውውር ምደባና የደመወዝ መሰረዙን የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንደገለጹት÷ በመጠናቀቅ ላይ ባለው በ2014 በጀት ዓመት የ25 ሺህ 990 የክልሉ የመንግስት ሠራተኞች ፋይል ተመርምሮ 4 ሺህ 155 ሕገ ወጥ የቅጥር ፣ ዝውውር፣ ምደባና የደመወዝ ማስተካከያ ስራዎች ተሰርዘዋል።
በተደረገው የሠራተኞች ፋይል ማጣራት ከ 614 በላይ ሰራተኞች በሀሰተኛ የትምህርትና የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ተመርምሮ ቅጥራቸው መሰረዙን ኃላፊው ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ በአሰራር ችግሮች ሊባክን የነበረ 82 ሚሊየን 887 ሺህ 682 ብር ማዳን መቻሉን ነው አቶ ዘይኔ የገለጹት፡፡
የሠራተኛው የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሻሻሉ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ኃላፊው መናገራቸውንም ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.