Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያስገነባውን የገርጂ መኖሪያ መንደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ18 ወራት ውስጥ አስገንብቶ ያጠናቀቀውን እና የፊታችን እሁድ የሚመረቀውን የገርጂ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር ጎብኝተዋል፡፡
ከንቲባዋ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት÷ በአጭር ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ግዙፍ ፕሮጀክት በከተማ መሰራቱ ለመዲናዋ ውበት እና እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የከተማውን የቤት ችግር ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ አልሚዎችን ከተማ አስተዳደሩ እንደሚያበረታታ መግለጻቸውንም ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.