Fana: At a Speed of Life!

ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምጻዊት እና የሙዚቃ ፀሃፊ ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) ዛሬ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆና ተመርጣለች፡፡

በዓለም አቀፍ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን የሴቶችን ቀን ምከንያት በማድረግ በተካሄደ የሹመት ስነ ስርዓት ላይ ድምጻዊት ብሩክታዊት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆና መመረጧ ይፋ ሆኗል፡፡

በዚህ ወቅትም ድምጻዊቷ “የስደተኞች ጉዳይ በጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆኜ በመመረጤ ኩራት እና ክብር ይሰማኛል፥ ለዚህ ጥሩ ዓላማም ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነኝ” ብላለች፡፡

ብሩክታዊት ጌታሁን በሙዚቃው ዘርፍ ጉልህ ሚና ያላት ወጣት ስትሆን አፍሪማን ጨምሮ ሌሎች ሽልማቶችን ማሸነፍ ችላለች።፡

እንዲሁም በቅርቡ በኦስሎ በተካሄደው 2019 የኖቤል ሽልማት ስነ ስርዓት ላይ ሃገሬ እና ሲንጃለዳ የተሰኙ ሙዚቃዎችን በመጫወት አድናቆትን አግኝታለች፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይም በመሳተፍ ትታወቃለች፡፡

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.