አቶ ደመቀ መኮንን አዲስ ከተሾሙት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሚካኤል ሀመርን ጋር ተወያይተዋል ።
በውይይታቸውም በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን እንዲሁም በግጭቱ ወቅት ለተፈጸሙ በደሎች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
አቶ ደመቀ በውይይቱ መንግሥት ወደ ትግራይ እርዳታ ለሚያጓጉዙ ሰብዓዊ አጋሮች ያልተገደበ ተደራሽነትን ለማመቻቸት ያለውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።