Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የመገጭ ግድብን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልልርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የመገጭ ግድብን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝት መርሐ ግብሩ የመገጭ ግድብ ግንባታ ሂደት የዛሬ ሁለት ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡

በ5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እየተገነባ ያለው ይህ ግድብ ከመስኖ ልማት ባሻገር የጎንደር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግርን በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከርዕሰ መስተዳድሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሥራ ተቋራጭነት በ2005 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ግድቡ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከታቀደለት የመጠናቀቂያ ጊዜ መዘግየቱ ተገልጿል።

የመገጭ ግድብ 185 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ እንደሚይዝ የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 116 ሜትር ኪዩብ የሚሆነው በጎንደር ዙሪያና ደንቢያ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች ለመስኖ ልማት የሚውል ነው ተብሏል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.