Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል በ2014 በጀት ዓመት ግንባር ቀደም ያላቸውን ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ሸለመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ በክልሉ በ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም በከፍተኛ ግብር ከፋይነት የተመዘገቡ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮችን ሸለመ፡፡

በሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ አዘጋጅነት በ2014 በጀት ዓመት ግንባር ቀደም ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን ለመሸለም የተዘጋጀው ሥነ- ሥርዓት በጅግጅጋ ከተማ ፣ ቀርያን ዶዳን መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው የተካሄደው፡፡

በዝግጅቱ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህ፣ የሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ-ናጂ መሐመድ፣ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ የከፍተኛ ግብር ከፋዮችና ነጋዴዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

መርሐ-ግብሩን የከፈቱት የሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ-ናጂ መሀመድ÷ የሽልማቱ ዋና ዓላማ የክልሉ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮችን መለየትና ማበረታታት እንደሆነ ተናግረዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ÷ የዓለም ሀገራትን ኢኮኖሚ ከሳደጉ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው የሀገሪቱ ህዝቦች ግብር ከፋይነትና የገቢያቸው መጠን ማደግ እንደሆነ ጠቁመው፣ የሶማሌ ክልል መንግሥትም ለገቢዎች ቢሮ አሰራር መዘመን ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ነው የጠቆሙት።

በዚህም የክልሉ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ የክልሉን የመሠረተ ልማት ዝርጋታ ማስፋፋት መቻሉን ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ ከግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች በተጨማሪ ከፍተኛ ገቢ ሰብሳቢዎችም መሸለማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.