Fana: At a Speed of Life!

ለአህጉራዊ ሰላም ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ተሞክሮ በመውሰድ መስራት አለባቸው -የኔፓድ ዋና ስራ አስፈጻሚ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአህጉራዊ ሰላም ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ተሞክሮ በመውሰድ በጋራ መደራጀትና መስራት እንዳለባቸው ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት (ኔፓድ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ናርዶስ በቀለ ገለጹ፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዋና መስሪያ ቤት የተገኙ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሠራዊት ዋና ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በተቋሙ የተሠሩ የለውጥ ሥራዎችን በተለይም ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል የሚገለገልባቸው ቴክኖሎጂዎችና ትጥቆች እንዲሁም የወንጀል ምርመራ ፎረንሲክ ዲፓርትመንት አዳዲስ የቴክኖሎጂ አቅሞችን ተዘዋውረው እንዲመለከቱ አድርገዋል ፡፡
የኔፓድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ናርዶስ በቀለ ከጉብኝቱ በኋላ እንዳሉት ፥ ለልማት ዋናው መሰረት ህግ ማስከበር መሆኑንና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እየተጠቀመበት የሚገኘው ቴክኖሎጂ ህግን ለማስከበር ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል፣ ሰላምን ለማስፈንና እድገትን ለማፋጠን በራስ አቅም ስራዎች መሰራቱ እንዳስደሰታቸው የገለፁት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ፥ የተመለከቱት ቴክኖሎጂ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተከናወነው ሪፎርም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆንና አፍሪካንም ጭምር ይዞ ሊወጣ እንደሚችል አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብቻዋን ሰላም ብትሆን የተሟላ ስለማይሆን ለአህጉራዊ ሰላም መረጋገጥ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን ተሞክሮ በመውሰድ በጋራ በመደራጀት መስራት ይኖርባቸዋል፤ አዲሱ አጋርነት ለአፍሪካ ልማት ለአፍሪካ እድገትና ትብብር አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.